
በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ባየር ሙኒክን 2 ለ1 አሸንፏል።
ሪያል ማድሪድ ባየርሙኒክን በድምር ውጤት 4 ለ 3 በማሸነፍ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ አልፏል።
ለሪያል ማድሪድ ሁለቱንም ግቦች ባለቀ ደቂቃ ተቀይሮ የገባው ሆሴሉ ሲያስቆጥር፤ ባየር ሙኒክን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ አልፎንሶ ዴቪስ አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ እና ቦርሲያ ዶርትመንድ በዌምብሌይ ስታዲየም የፍፃሜ ጨዋታቸውን ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ያደርጋሉ።
EBC
More Stories
ሪያል ማድሪድ የዓለማችን ውዱ ክለብ ሆነ
ፒኤስጂ በተከታታይ ለ2ኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሸነፈ
ክሪስታል ፓላስ የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!