August 22, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሀል ሲቲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

ማንችስተር ዩናይትድ የዓመቱን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ልግ ውድድር ዛሬ ከሀል ሲቲ በሚያደርገው ጨዋታ ሲጀምር ወደ ፕሪሚየረ ሊጉ የተመለሰው ሃል ሲቲ በሊጉ ለመቆየት የሚያደርገውን ትግል በሜዳው ኤምኬኤም ዩናይትድን በማስተናገድ ይጀምራል፡፡

8 ሰዓት ከ30 በሚጀመረው ጨዋታ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ያስፈረማቸውን ዮሪ ቴሊማንስ እና አንድሬ ሳንቶስን በቋሚነት እንደሚጠቀም ይጠበቃል፡፡

በጨዋታው ሜስን ማውንት በጉዳት ምክንያት የመሰለፉ ነገር ያልተረጋገጠ ሲሆን በተመሳሳይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝም በጉዳት ከስብስቡ ውጪ ነው፡፡

ምሽት 1 ሰዓት ከ 30 ደግሞ ቶተንሀም ሆትስፐር ከሜዳው ውጭ ከብሬንትፎርድ ይጫወታል፡፡ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ፣ ኢፕስዊች ታውን ከ ሰንደርላንድ እና ኖቲንግሀም ፎረስት ከ ሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ 11 ስዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡