የኢንተር ማያሚው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በሜጀር ሊግ ሶከር ጨዋታ ላይ የፊላዴልፊያ ዩኒየኑን ተጫዋች ኪዊን ሱሊቫንን በጥፊ በመምታቱ የገንዘብ መቀጮ ተጥሎበታል።
ኢንተር ማያሚ ከፊላዴልፊያ ዩኒየን ጋር 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ባጠናቀቁበት ጨዋታ የ39 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ተጫዋቹ በክርኑ መታኝ በሚል በጨዋታው መገባደጃ ላይ ከበስተጀርባ የሱሊቫንን እራስ በጥፊ መትቶታል።
ሜሲ አባቱ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ የመጀመሪያ ግቡን በዚሁ ጨዋታ ማስቆጠር ቢችልም ድርጊቱን ተከትሎ በሜጀር ሊግ ሶከር አደራጅ አካል የገንዘብ ቅጣት የጣለበት ሲሆን፣ የቅጣቱ መጠን ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም።
በዚሁ ውጥረት በነገሰበት ጨዋታ ላይ የሜሲ የቡድን አጋር ኢያን ፍሬይ የሱሊቫንን አንገት በመያዙ ሌላኛው የተቀጣ ተጫዋች ሆኗል። በጨዋታው ጭማሪ ሰዓት የኢንተር ማያሚው ያኒክ ብራይት እና የኪዊን ሱሊቫን ወንድም ካቫን ሱሊቫን በሁለት ቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣታቸው ተጠናቋል።
ሆኖም ከጨዋታው በኋላ በተደረገ ግምገማ በካቫን ሱሊቫን ላይ ተጥሎ የነበረው የአንድ ጨዋታ እገዳ መነሳቱ ተገልጿል።
More Stories
ሀል ሲቲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ
ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በሰሜን ለንደን በተደረገው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታ ሻምፒዮኑ አርሰናል አዲሱን አዳጊ ቡድን ኮቬንትሪ ሲቲን በ3 የግብ ልዩነቶች አሸንፏል።
ፒኤስጂ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ሻምፒዮን ሆነ