በየዓመቱ ሐምሌ 19 ቀን የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እና በሐዋሳ ከተማ በሃይማኖታዊ ሥርዓት በመከበር ላይ ይገኛል።
በዓሉ የሃይማኖት አባቶች፣ ምዕመናን እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት እንግዶች በተገኙበት በመንፈሳዊ ሥርዓት እየተከበረ ነው።
በቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እየተካሄደ ባለው የንግሥ በዓል ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የንግሥ በዓል ላይ ደግሞ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ተገኝተው በዓሉን ከምዕመናን ጋር በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ።
More Stories
አንዳንድ ደማቅ ድሎች በጦር ሜዳ አይመዘገቡም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የመዝጊያ መርሀ ግብር
የተሻለች ሀገር ለትውልድ የማሸጋገር ርዕይ – ሀገራዊ ምክክር