የሀገራዊ ምክክሩ 80 ንዑሳን ቡድኖች በስምንቱ አጀንዳዎች ላይ ምክክር እያደረጉ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር ገለፁ።
ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር በሰጡት መግለጫ፤ 4000 አባላት የያዘው የሀገራዊ ምክክር ጠቅላላ ጉባኤ ወደ 8 ትልልቅ የስራ ቡድኖች የተከፈለ ሲሆን እያንዳንዱ የስራ ቡድን በውስጡ 500 ተሳታፊዎች ይዟል።
አንድ የስራ ቡድን ወደ 2 ስልታዊ ቡድኖች ይከፈላል፣ እያንዳንዱ ስልታዊ ብድን 250 ተሳተፊዎች ይዟል። 250 ተሳታፊዎች የያዘው ቡድን ወደ 50 ተሳታፊዎች ወደያዘ 5 ንዑስ ቡድኖች ተመድበዋል። በመጨረሻም አንድ ንዕስ ቡድን ወደ 5 ጥቃቅን ቡድኖች ሲከፈል እያንዳንዱ ቡድን 10 ተሳታፊዎች በውስጡ የሚይዝ መሆኑን አብራርተዋል።
በአጠቃላይም በ80 ንዕሳን ቡድኖች በመከፋፈል በአጀንዳዎች ላይ ምክክር እያደሰጉ ሲሆን 160 አመካካሪዎችና 256 ቃለጉባኤ ፀሀፊዎች የተሰማሩ መሆንን ገልጸው፣ የሌላውን የሚሰሙበትና የሚያስተናግዱበት ሂደት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ይህም ሂደት ፈጠራን፣ተሳትፎንና ለሁሉም የተሻለ ምክረሀሳቦችን ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ መሆኑን ገልጸው፣ በምክክር ሂደቱ ውስጥ ቁልፍ አካል መሆኑን ገልፀዋል።
#ጋዜጣ ፕላስ
More Stories
አንዳንድ ደማቅ ድሎች በጦር ሜዳ አይመዘገቡም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የመዝጊያ መርሀ ግብር
የተሻለች ሀገር ለትውልድ የማሸጋገር ርዕይ – ሀገራዊ ምክክር