የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ አስከሬን በኢራቅ ናጃፍ ከተማ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በክብር እየተከናወነ ባለበት ወቅት አሜሪካ እና ኢራን አዲስ ጥቃት ከፍተዋል።
ታዛቢዎች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚጓዙ መርከቦች ቁጥር “በአስደናቂ ሁኔታ ቀንሷል” ሲሉ ሪፖርት አድርገዋል።
አሜሪካ 90 ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቷን ስትገልጽ፥ አንዳንዶቹ በባሕረ ሰላጤው አቅራቢያ የተፈጸሙ ናቸው ተብሏል።
ኢራን ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ14 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቃለች።
የመንግስት ሚዲያዎች እንደዘገቡት የቡሼህር የኑክሌር ኃይል ማመንጫ አቅራቢያ የጥቃቶቹ ኢላማ መሆኑ ተነግሯል።
አሜሪካ አዲሱን ጥቃት በተመለከተ አስያያየት ከመስጠት ተቆጥባለች።
ኢራን በአጸፋው በኩዌት፣ ባህሬን እና ኳታር የሚገኙ የአሜሪካ ንብረቶችን ተጨማሪ ጥቃት ማድረጓን በማሳወቅ ጥቃቱንም አጠናክሬ እቀጥላለሁ ብላለች።
አሜሪካና ኢራን አያቶላ አሊ ኻሜኒ በሚቀበሩበት ወቅት የጀመሩት ጥቃቶች ተጠናክረው ቀጠሉ ።
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ