በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሚከሰተው የመድሃኒ እጥረትና የዋጋ ውድነት የሚታደጋቸው የህዝብ ፋርማሲ በመከፈቱ እፎይታ እንደተሰማቸው አስተያየት የሰጡት የከተማው ነዋሪዎች አሰራሩ ግልጽና ተጤቂነት ያለው እንዲሆን ጠይቀዋል፡
ከ20 ዓመት አስቀድሞ የማሻ ከተማ የህዝብ መዲሐሀኒት ቤት እንደነበረው ያስታወሱት የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንዷአለም ጌታቸው ዛሬ ላይ በብዙ ጥረት የህዝብ መድሀኒት ቤት ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ዘርፌ ፋይዳ እንዳለው አለው አብለዋል፡፡
በከተማ ደረጃ ሌደራጀው የህዝብ መድሀኒት ቤት እገዛና ድጋፍ ላደረጉ ባለድረሻ አካላት ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባው አገልግሎቱን ይበልጥ ለማዘመን ከመንግሰት ጤና ተቋም ጋር በመነባበብ እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡
በከተማው የህዝብ መዲሃኒት ቤት ባለመኖሩ መድሀኒት ፍለጋ የሚደረግ ውጣ ወረድ አድካሚ እንደ ነበር ያስታወሱት ከከተማው ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ አቻየሽ እሞ እና ወይዘሮ ዓለምጸሐይ ፀጋዬ ናቸው፡፡ ይሁንና አገልግሎቱ ከመንግሰት የተወሳሰበ አሰራር የተላቀቀና ቀልጣፋ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
መዲሀኒት መደብሩ በይፋ ስራ ከጀመረ በኋላ አገልግሎቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ከማግኘት ባሻገር ወደ ሌሎች አካባቢዎች ይደረግ የነበረውን እንግልት በማስቀረቱ መደሰታቸውንም አክለዋል፡፡
የማሻ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢለሳ ሞገስ ህዝቡን በጤና ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተሠራው ተግባር ውጤታማ ስራ መከናወኑንና አገልግሎቱን በይበልጥ ለማጠናከር በቀጣይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።
የነዋሪውን ኢኮኖሚ የሚዶግም የህዝብ መድሀኒት ቤት ከፍቶ በይፋ ስራ ማስጀመሩን የማሻ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ