July 11, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

እንግሊዝ ከኖርዌይ፤ አርጀንቲና ከስዊዘርላንድ …

አሜሪካካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ጥምር አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ይካሄዳሉ።

ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ በሚገኘው 23ኛው የዓለም ዋንጫ ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ለመለየት ዛሬ ኖርዌይ ከእንግሊዝ እንዲሁም አርጀንቲና ከስዊዘርላንድ ብርቱ ፍልሚያ ያደርጋሉ።

በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩብ ፍፃሜ የበቃችው እና በውድድሩ አስደናቂ ብቃት እያስመለከተች የምትገኘው ኖርዌይ ለ11ኛ ጊዜ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዋን ከምታደርገው እንግሊዝ ጋር ትጫወታለች።

ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ጨዋታ ሌሊት 6:00 ላይ በሚያሚ ስታዲየም ይካሄዳል።

እንዲሁም አርጀንቲና በ39 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ እየተመራች በካንሳስ ሲቲ ስታዲየም ከስዊዘርላንድ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ንጋት 10:00 ላይ ይደረጋል።

በጨዋታው ከ72 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩብ ፍፃሜው ያለፈችው ስዊዘርላንድ አዲስ ታሪክ ለመስራት የምታደርገው ፍልሚያ ለአርጀንቲና ከባድ ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል።