የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 51ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡
በዚህም መሠረት የቀረቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን በግብርና 18፣ በኢንዱስትሪ 1 በአጠቃላይ 2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎችን መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።
በሁለተኛ አጀንዳነት በተለያዩ ረቂቅ ደንቦች ላይ የተወያየ ሲሆን በዚህም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቨሽን ካውንስል ማቋቋሚያ ደንብን እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአከባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ደንብን መርምሮ አጽጽቋል።
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 51ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
More Stories
የባህር በር – የኢትዮጵያ የፍትህና የልማት ጥያቄ
የኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጥሪ
በምክክሩ ለሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በነጻነት ተወያይተናል – ተመካካሪዎች