የቅድመ ምረቃ በረራው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኤርፖርቶች ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጌታነህ አደራ ጨምሮ ሌሎች የአየር መንገዱ ከፍተኛ ማኔጅመንቶች እንዲሁም የክልል፣ የቤንች ሸኮ ዞንና የሚዛን አማን ከተማ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው በይፋ የጀመረው።
የበረራ አገልግሎቱ መጀመር በአካባቢው ነዋሪዎች፣ ተጓዦችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሚዛን አማን ከተማ በሳምንት ሦስት ቀናት የበረራ መርሐግብር እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፣ በረራው ለማኅበረሰቡ ፈጣን፣ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት ጉዞ አገልግሎት ለማቅረብ ያግዛል።
በተጨማሪም የንግድ፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን በማነቃቃት ለሚዛን አማን ከተማ ብሎም ለመላው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለማሕበራዊ ትስስርና ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ከሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሚዛን አማን ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ ጀምሯል።
More Stories
የነገ ትውልድ ተስፋ አረንጓዴ ልማትና ቱሪዝም
ህገ ወጥ የቡና ግብይት ቁጥጥርን ማጠናከር እንደሚገባ የካፋ ዞን ምክር ቤት አሳሰበ ።
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ የአቮካዶ ምርቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እያደረጓት ነው