ዜጎች ድምጽ ለመስጠት ወደ ተመዘገቡበት የምርጫ ጣቢያ ሲያመሩ የሚከተሉትን አስፈላጊ ነገሮች መያዝና ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ፣
የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ፣
በመራጮች ምዝገባ ወቅት የተረጋገጠበት ሌላ ሰነድ ያላት/ው ወይም ማንነትዎ በምርጫ ምዝገባ ወቅት በምስክሮች ስለመረጋገጡ በመራጮች መዝገብ ላይ የሰፈረ፣
የመራጮች መዝገብ ላይ ስሙ የሰፈረ፣
ድምጽ ያልሰጡ መሆኑ ሲረጋገጥ ድምጽዎን የመስጠት መብት አለዎት፣
እንዲሁም የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ የጠፋበት መራጭ ጉዳዩን ለምርጫ ጣቢያው በማስረዳት ማንነቱን እንዲሁም በመዝገቡ ላይ ስሙ የሰፈረና ያልመረጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ጉዳዩ በቃለ ጉባዔ ተይዞ እንዲመርጥ ይደረጋል፡፡
More Stories
የባህር በር – የኢትዮጵያ የፍትህና የልማት ጥያቄ
የኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጥሪ
በምክክሩ ለሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በነጻነት ተወያይተናል – ተመካካሪዎች