”ብልጽግና ፓርቲ በሀገራችን ያስመዘገባቸውን ስኬቶች ለማስቀጠል በሙሉ አቅማችን እንደግፋለን” ሲሉ የሰልፉ ታዳሚዎች ገልጸዋል ።
በሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን ያረጋገጠ፣ በሪፎርም የመጣ፣ ያለፉ መልካም እሴቶችን ያስቀጠለና ጉድለቶችን ያረመ እንዲሁም የወንድማማችነትን እሴት ያጎለበተ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል።
ብልፅግና ፓርቲ በዞኑ የነበረውን የሰላም ችግር በመደመር እሳቤ በመፍታት ወንድማማችነት ያፀና መሆኑን የገለጹት አቶ አበበ፤ ይህም ህዝቡ ወደ ልማት እንዲገባና ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ አስችሏል ብለዋል።
ለዘመናት የጌጫ ከተማ ህዝብ ጥያቄ የነበረው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ምላሽ ያገኘበት፣ ለባህላዊ እውቀቶች እውቅና የተሰጠበት እንዲሁም መለስተኛ የሆስፓታል ግንባታ ለመገንባት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለው በብልፅግና ፓርቲ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ፓርቲው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ህዝቡ በመጪው ምርጫ የፓርቲውን ምልክት የስንዴ ነዶን በመምረጥ ድጋፉን እንዲገልጽ ጥሪ አቅርበዋል
የብልፅግና መንግስት በኢትዮጵያ ደረጃ በርካታ ለውጦችን እያስመዘገበ መሆኑን የገለፁት የሸካ ዞን ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊና በማሻ ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት እጩ ተወካይ ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ በዞናችን በግብርና፣በጤናና ለሎች ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
በዞናችን ውስጥ የነበረውን የፀጥታ ችግር በመቅረፍ ህዝባችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ፓርቲ ነው ያሉት ወ/ሮ ትዕግስት የተጀመሩ የድልድይና መንገድ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ በግንቦት 24 ፓርቲውን በመምረጥ ድጋፉቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል ።
ከብልፅግና ፓርቲ በፊት የነበረው የአካባቢ እድገት ውጤታማ እንዳልሆነ የገለፁት የዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አዝመራ አንደሞ በብልፅና ፓርቲ በዞናች የመጣውን ለውጥ ማስቀጠል አለብን ብለዋል።
በዞኑ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ እንዲሁም ለሎች ፕሮጀክቶች እንዲጀመሩ የብልፅግና ፓርቲን በመምረጥ ድጋፋቸውን እንዲያሳዩም ጠቁመዋል ።
ባለፉት አምስት አመታት ዠ እንደ ሀገር በርካታ ተግባራት በመፈጸም የሀገራችንን ሉአላዊነት ማስጠበቅ ችሏል ያሉት የሰልፉ ታዳሚዎች በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች የመጡ ለውጦች ቀላል አይደለም ብለዋል።
የህዝቡ የዘመናት ጥያቄ ሆኖ የቆየው የመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፓርቲው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ደጋፊዎች የጌጫ ከተማ ነዋሪዎችን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር በመቅረፍ ተጠቃሚ ማድረጉንም ተናግረዋል ።
የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፓርቲው የገጠር መንገድ ተደራሽ በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል ።
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ጽኑ ድጋፍና አጋርነት በወሰዱት ካርድ ለማረጋገጥ መዘጋጀታቸውንም ደጋፊዎች ገልጸዋል ።
በዕለቱ የታደሙት ደጋፊዎች የፓርቲውን የምርጫ ምልክትና የተለያዩ አገራዊ መፈክሮችን በማንገብ፣ በቀጣይ ለሚከናወኑ የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች ከመንግስትና ከፓርቲው ጎን በቁርጠኝነት እንደሚቆሙ ተናግረዋል ።
7ኛው አገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ነፃና ፍታሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡም ጠቁመዋል።
More Stories
ጋዜጠኞች ሙያቸውን እና ሕግን እንዴት መከተል እንዳለባቸው ሊያውቁ ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።