መሬት ያለ እረፍት በደቂቃ 27.7 ኪሎ ሜትር (በሰዓት ከ1,600 ኪሎ ሜትር በላይ) በራሷ ዛቢያ ላይ ትሽከረከራለች። እስቲ አስቡት፤ ይህን ያህል ፍጥነት እያላት በድንገት “ቆም” ብትል ምን ሊፈጠር ይችላል? ውጤቱ አስከፊና ምናባዊ ከሚመስል አደጋ በላይ ነው።
ልክ በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ያለ መኪና ድንገት ፍሬን ሲይዝ በውስጡ ያለ ሰው ወደ ፊት እንደሚወረወረው ሁሉ፣ መሬትም በድንገት ብትቆም በላዩዋ ላይ ያለን እኛ ሰዎች፣ ቤቶች፣ ተሽከርካሪዎች እና ተራራዎች ጭምር በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምስራቅ አቅጣጫ እንወረወራለን።
መሬት ወደ ምስራቅ እየተጓዘች በመሆኑ፣ እርሷ ብትቆምም እኛ ግን በነበረን ፍጥነት ጉዟችንን ስለምንቀጥል ከመሬት አካል ላይ ተፈንጥረን እንወጣለን።
አደጋው በዚህ ብቻ አያበቃም፤ የውቅያኖስ ውሃዎች ሁሉ ካሉበት ተነቅለው ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ግዙፍ ማዕበልና ሱናሚ ምድርን ያጥለቀልቋታል። መሬት ለአንድ ዓመት መሽከርከር ብታቆም ደግሞ ወቅቶችና የሌሊትና ቀን ዑደት ይናጋል።
ለስድስት ወራት ያህል በአንድ በኩል ያለው የምድር ክፍል የፀሐይ ንዳድ ውስጥ ስለሚቆይ ይቃጠላል፤ ቀሪው ስድስት ወር ደግሞ በሌላኛው በኩል ድቅድቅ ጨለማና የማይቻል ቅዝቃዜ (በረዶ) ይነግሳል።
መሬት ያለ እረፍትና በጥንቃቄ መሽከርከሯ ለእኛ ለሰው ልጆች ህልውና የተሰጠ ትልቅ ስጦታ መሆኑን የሳይንስ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።