በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሂልተን ሆቴል በተካሄደው የኋይት ሃውስ የዘጋቢዎች ማኅበር ዓመታዊ የእራት ግብዣ ላይ፣ የተኩስ ድምጽ በመሰማቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደህንነት አባላት ታጅበው በአስቸኳይ ከመድረክ እንዲወጡ ተደርጓል።
በወቅቱ በስፍራው የነበሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና በርካታ የካቢኔ አባላትም በፍጥነት ከአካባቢው ተወስደዋል።
የአሜሪካ የደህንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ፣ ፕሬዝዳንቱ እና ምክትል ፕሬዝዳንቱ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑንና አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ’ትሩዝ ሶሻል’ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተኳሹ መያዙን ገልጸው ለህግ አስከባሪዎች ፈጣን እና ደፋር እርምጃ ምስጋና አቅርበዋል።
በስፍራው የነበሩት የሲኤንኤን ጋዜጠኞችም ተኳሹ በጥቂት እርምጃዎች ርቀት ላይ እንደነበር የገለጹ ሲሆን፤ ድርጊቱ እጅግ አስደንጋጭ እንደነበር ዘግበዋል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።