የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ሁለተኛው ዙር ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ በፓኪስታን ሊካሄድ እንደሚችል መናገራቸውን ኒው ዮርክ ፖስት ዘግቧል።
ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ለጋዜጣው በስልክ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ “በእውነቱ እዚያው ኢስላማባድ ብትቆዩ ይሻላል፤ ምክንያቱም በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ አንድ ነገር ሊከሰት ይችላል፤ እኛም ወደዚያ የመሄድ ዝንባሌ አለን” ብለዋል።
ይህ አስተያየት የተሰጠው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቀደም ሲል ሁለተኛው ዙር ቀጥተኛ ድርድር በአውሮፓ ውስጥ የሆነ ቦታ ሊካሄድ እንደሚችል ጠቁመው ነበር። ሆኖም ኒው ዮርክ ፖስት እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንቱ ቆየት ብለው በድጋሚ በደወሉበት ወቅት ድርድሩ ወደ ኢስላማባድ የመመለስ ዕድሉ “ከፍተኛ” መሆኑን ገልጸዋል።
በዚሁ ንግግራቸውም የፓኪስታኑን የጦር አዛዥ አሲም ሙኒርን “ጥሩ ሥራ እየሠሩ ነው” ሲሉ አድንቀዋል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።