March 26, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

‎የእናቶችንና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።



‎5ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ እና የማህፀን በር ካንሰር በሽታ መከላከያ ክትባት የንቅናቄ መድረክ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ተካሂዷል።

‎መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የማሻ ከተማ ከንቲባ አስተደደር አቶ አንዷለም ጌታቸዉ የማህፀን በር ካንሰር መለየት እና 5ኛ ዙር የፖልዮ ክትባት ዘመቻ በማድረግ አግባብ ባለዉ መልክ ሲራዉ ስከታማ እንድሆን የባለድርሻ አካላት ርብርብ በተቀመጠዉ ግዜ ሰለዳ እንድጠናቀቅ መልዕክታቸዉን አስተላልፏል።

‎የማሻ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ኢለሣ ሞገስ በበኩላቸዉ በሀገራችን ደረጃ በዋናነት ለእናቶች ሞት ምክንያት የሆነው የማህፀን በር ካንሰር በመሆኑ ዕድሜያቸው ከ 9 ዓመት በላይ የሆኑ ህፃናትን በማስከተብ በሽታውን ለመከላከል መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉም ገልፀዋል።

‎5ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በቀን 18 ጀምሮ በመደበኛና ቤት ለቤት ስለሚሰጥ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን በማስከተብ ህፃናትን ከበሽታው እንዲታደጉም ተናግረዋል።

‎የፖሊዮ ክትባት አላማዉ በመደበኛው የክትባት መረሀ ግብር ክትባት ሳይወስዱ የቀሩና ጀምረዉ ያቋረጡ እድመያቸዉ ከ-5 ዓመት በታች የሆኑ ሁሉንም ህፃናት የክትባት አገልግሎት እንድያገኙ ለማድረግ ይረዳል ።

‎ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘመቻዉ የተሳካ እንድሆን በፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ወቅት የምሰሩ ስራዎችን በጋራ ማቀድ መከታተልና መገምገም ያስፈልጋል ብለዋል የሸካ ዞን ጤና መምርያ በሽታ መከላከል መቆጣጠር እና የአከባቢ ጤና አገልግሎት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ አባይነሽ ደንበሎ ።

‎የፖሊዮ ቫይረስ ተላላፊ በሽታ ሲሆን ከንፅህና ጉድለት የሚመጣና ለሽባነት የሚያጋልጥ በሽታ ነዉ፣በተለይ ህፃናትን የሚጎዳ ሆኖ በእግር ወይም እጅን በማልፈስፈስ ሊያስከትል የሚችል በሽታ መሆኑን ገልፀዋል።

‎በውይይቱ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ቅድመ-መደበኛ ተማርዎች ላይ እና ትምህርት ቤቶች ላይ መረጃ ተደራሽ ማድረግ እንደምያስፈልግ ገልፀዉ፣ የማህፀን በር ካንሰር በጊዜ ክትባት ካገኘ በሽታውን መቆጣጠር ስለሚቻል ዕድሜያቸው የደረሱትን በማስከተብ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ተናግረዋል።

‎በውይይት መድረኩ የኃይማኖት አባቶች ፣ከሁሉም ጤና ጣቢያ የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ፣የከተማ አስተዳደር አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች እንድሁም ጥር የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል ።