ማሻ፤ መጋቢት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የነበችውን ሴኔጋልን ውጤት በመሰረዝ ክብሩን ለሞሮኮ መስጠቱን ይፋ ካደረገ በኋላ በዓለም እግር ኳስ ላይ መነጋጋሪያ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
120 ደቂቃ በወሰደው እና አውዘጋቢ ጉዳዮች የነበሩበት የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ለ17 ደቂቃ ከተቋረጠ በኋላ በቀጠለው መርሀ ግብር ሴኔጋል 1 ለ 0 አሸንፋ ዋንጫውን ወስዳ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ከዚሁ ጋር በተገናኘ የወቅቱ የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የቀድሞው የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኦጉስቲን ሴንግሆር ለቢቢሲ እንደተናገሩት ካፍ ያሳለፈው ውሳኔ እጅግ አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡
እግር ኳስ የሚያልቀው በሜዳ ላይ እንጂ በቢሮ ውስጥ በተደረገ ስምምነት አይደለም ያሉት ስራ አስፈጻሚው “ካፍ የወሰደው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው ነው። አንድ ኮሚቴ የካፍን ደንቦችና የፊፋን የእግር ኳስ ህግጋት በመጣስ ዋንጫውን ከሴኔጋል ነጥቆ ለሞሮኮ ሲሰጥ ማየት በጣም አሳፋሪ ነገር ነው። ይህንን ማውገዝ አለብን” ብለዋል፡፡
እንዲህ ያለ ነገር በአፍሪካም ሆነ በአለም እግር ኳስ ታሪክ ሲከሰት የመጀመሪያው ነው ያሉት የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኦጉስቲን ሴንግሆር ሴኔጋል ጉዳዩን ወደ አለም አቀፍ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የወሰደችው በመሆኗ እንደምታሸነፍ እና ዋንጫም ከእጇ እንደማይወጣ እርግጠኛ ነኝ ብለዋል፡፡
More Stories
ቦርንማውዝ ከ ማንችስተር ዩናይትድ
31ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ነገ ጀምሮ ይካሄዳሉ!
ማንቼስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ…