ማሻ፤ መጋቢት 6/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ሶስተኛ ሳምንቱን በያዘው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ፍጥጫው አሁንም ቀጥሏል። ኢራን በባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የሚሳኤል ጥቃትፈፅማለች።ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ የሆርሙስ የባህር ወሽመጥ ክፍት እንዲሆን ሌሎች አገሮችም የጦር መርከቦችን እንዲልኩ ጠይቀዋል።
ሶስተኛ ሳምንቱን በያዘው አሜሪካ እናእስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ፍጥጫው አሁንም ቀጥሏል። ኢራን በባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ግቢ የሚሳኤል ጥቃት የፈፀመች ሲሆን፤ ከአሜሪካ ጋር የተያያዙ የሀይል መሰረተልማቶች ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር ዝታለች።ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ሁለት ሺ የሚበልጡ የባህር ኃይል ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ማሰማራቷን ገለፃች።ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን በቀጠሉበት እና ኢራን በባህረሰላጤው ሀገራት የነዳጅ እና የኃይል መሠረተ ልማቶችን ማጥቃቷን በቀጠለችበት በአሁኑ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ወደ 2,500 የሚጠጉ የአሜሪካ የባህር ኃይል ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ማሰማራቷን ገልፃለች።ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት እንዳሉት የኢራንን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ጭነቶችን የማስተጓጎል ስጋት ሀገራቸው እየፈታች በመሆኑ ስጋት ሊሆን እንደማይገባ ገልፀዋል።የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የሆርሙስ የባህር ወሽመጥ ክፍት እንዲሆን ሌሎች አገሮችም የጦር መርከቦችን እንዲልኩ ጠይቀዋል። ፕራምፕ ትሩዝ ሶሻል በሚባለው የግል ማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንደፃፉት ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታላቋ ብሪታንያ እና ሌሎች አገሮች እንደሚሳተፉ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል። “በአንድ ሆነ በሌላ መንገድ የሆርሙስ ወሽመጥ በቅርቡ ክፍት ይሆናል”ም ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢራን በባህረ ሰላጤው ሀገሮች ላይ የምትሰነዝረውን የአየር ጥቃት ዛሬም ቀጥላ ነው የዋለችው።የሳውዲ አረቢያ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ማለዳ እንዳስታወቀው በዮርዳኖስ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝና ብዙም ሕዝብ በማይኖርበት የአል-ጃውፍ ክልል ውስጥ አንድ ድሮን መትቶ መጣሉን አስታውቋል።ሚኒስቴሩ ወደ ምስራቃዊ ክልል የሚያመሩ ሌሎች ሰባት ድሮኖችን መትቶ መጣሉን ተናግሯል፤ ይህም በኢራን አቅራቢያ ካሉት የሀገሪቱ ዋና ዋና የነዳጅ ማመንጫዎች አንዱ ነው። የኳታር፣ የመከላከያ ሚኒስትርም ለተሰነዘረበት የሚሳኤል ጥቃት ምላሽ መስጠቱን ገልጿል።በዱባይም በከተማው መሃል በሚገኝ አንድ ሕንፃ ፊት ለፊት ጥቃት መድረሱ ተዘግቧል።ያም ሆኖ አደጋው ምንም አይነት ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር መዋሉም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ሃማስኢራን በአረብ ጎረቤቶች ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት እንድታቆም ጥሪ አቅርቧል።
(DW)
More Stories
የአሜሪካ ነዳጅ ጫኝ የጦር አውሮፕላን በኢራቅ ተከሰከሰ
ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
ጦርነቱ በምን ሊቆም ይችላል ? የኢራን ስልታዊ እጅ መጠምዘዣ ጦርንት!