ማሻ፤ መጋቢት 1/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነት በዞኖችና በከተማ አስተዳደሮች ለማስፋት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውም ተጠቁሟል።
የክልሉ መሶብ አንድ ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት አዳሮ እንደገለጹት በክልሉ ሚዛን-አማን ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ለሕብረተሰቡ በሰፊው አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በማዕከሉ አምስት የክልልና አራት የፌዴራል ተቋማት 35 የተለያዩ አገልግሎቶች እየተሰጡ የሚገኙ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አስራት ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጥቅምት ወር ወዲህ 17 ሺህ 800 ዜጎች አገልግሎት ማግኘታቸውን አስረድተዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከሕብረተሰቡ ሲነሳ የነበረውን እንግልት እና ብልሹ አሰራሮችን በሰፊው እየቀረፈ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።
አገልግሎቱ በተቀመጠ ስታንዳርድ መሠረት በዲጂታል የሚከናወን በመሆኑ አላስፈላጊ ምልልሶችን በመቅረፍ ጊዜ፤ የሚወጣ ሀብትና ጉልበት መቆጠብ እንዳስቻለም አቶ አስራት አብራርተዋል።
በትራንስፖርት፤ በፍትህ በሌሎች ዘርፎች ተጨማሪ አገልግሎት መሰጠት የሚያስችሉ ሶፍትዌሮች የማበልጸግ ስራ እየተከናወነ መሆኑ የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ በክልሉ ለማስፋት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
የማዕከሉን አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት ለማስፋት በዞን ደረጃ የማዕከሉ ግንባታ ስራ የተጀመረ መሆኑን የገለፁት አቶ አስራት ግንባታው በሌሎች 15 ከተማ አስተዳደሮች የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
በማዕከል አገልግሎት በማግኘት ላይ እያሉ ያነጋገርናቸው ባለጉዳዮች በበኩላቸው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የዜጎችን ጊዜ፤ ጉልበትና ወጪ መቆጠብ ያስቻለ ነው ብለዋል።
አገልግሎት አሰጣጡ በዲጂታል አሰራር የሚከናወን በመሆኑ ከፌዴራል እስከ ክልል ያሉ ጉዳዮቻቸውን በአንድ ጊዜ ለማስፈፀም ያስቻለ በመሆኑ ከአላስፈላጊ እንግልት መታደጋቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
#SWMN
ማዕከሉ ስራ ከጀመረ ወዲህ 17 ሺህ 800 ዜጎች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት አግኝተዋል_አቶ አስራት አዳሮ
More Stories
ጦርነቱ በምን ሊቆም ይችላል ? የኢራን ስልታዊ እጅ መጠምዘዣ ጦርንት!
በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ በሬድ ፕላስ ኢንቨስትመንት ፕሮግራም ውስጥ በመሆን በአሳታፊ ደን አስተዳደር ማህበር የተደራጁ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገለፁ።
የኢራን አዲሱ መንፈሳዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ …