ማሻ፤ የካቲት 30/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአዲሱ የኢራን ሁለንተናዊ መሪ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።
ሞጅታባ ኻሚኒ በመመረጣቸው ደስ ብሎኛል ያሉት ፑቲን ሁል ጊዜም ከቴህራን ጎን ነን በሚልም አረጋግጠዋል።
ፑቲን አዲሱ መሪ ያባታቸውን ስራ እንደሚያስቀጥሉት እርግጠኛ እንደነበሩም ክሬምሊን አሳውቋል።
በአስቸጋሪው ወቅት ከኢራን ህዝብ ጋር በመሆን አገራቸውን ሞጅታባ እንደሚያስቀጥሉ የፕሬዚዳንቱ እምነት እንደሆነም ተነግሯል።
ሩሲያ ከቴህራን ጎን መቆሟን እንደምትቀጥልም ፕሬዚዳንት ፑቲን አረጋግጠዋል።
ቭላደእሚር ፑቲን የማይናወጥ ድጋፍቸው እንደሚቀጥልና ሞስኮ ለኢራን ወዳጆቿ ያላትን ብር ቱ አጋርነትም አረጋግጠዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ