ለዘመናት በሴራ እና በስህተት የታሰረው የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት፣ ዛሬ አዲስ መልክ ይዞ ብቅ ብሏል።
ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ መተንፈሻዋ የሆነውን የባሕር በር አማራጭ ስትነጠቅ መልክዓ ምድሯ ብቻ ሳይሆን ዜጎቿም ስለ ጉዳዩ እንዳይተነፍሱ ተደርገው ነበር።
ተከድኖ የበሰለው ጉዳይ ዛሬ ላይ የታሪክ ስህተትን በሚያርመው በሕጋዊ እና በሰጥቶ መቀበል ዲፕሎማሲ በጋለ መልኩ ወጥቷል።
የቀድሞ የባሕር ኃይል አባል የሆኑት ሲኒየር ቺፍ ተፈሪ መኮንን፣ “የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ተፈጥሮ እና ጂኦግራፊ እንደሚደግፈው የተገነዘበው ይህ ትውልድ፣ ጉዳዩን ታሪክም የሚመሰክርለት ስለመሆኑ ሊረዳ ይገባል” ይላሉ።
የባሕር በር ባለቤት የነበረችው ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ መርከቦች እንደነበሯት፤ የወጪ እና ገቢ ንግዷንም ታሳልጥበት እንደነበር ለኢቲቪ ተናግረዋል።
ከዚህም ባለፈ የአካባቢው ደኅንነት እንዲጠበቅ ያላለሰለሰ ሚና እንደነበራት አስታውሰዋል።
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በበኩላቸው፣ ጉዳዩን የፖለቲካ ፍጆታ ለማስመሰል የሚሞክሩ አካላት ስለመኖራቸው አመላክተው፣ ጥያቄው ከለውጡ በፊትም ይነሣ የነበረ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ እንደነበር አመላክተዋል።
ይህ ጉዳይ ተራ የፖለቲካ አጀንዳ ሳይሆን የታሪክ ስህተት የሚታረምበት፣ የ130 ሚሊዮን ሕዝብ ሕልውና እና የነገ ብልጽግና ማረጋገጫ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውታል።
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ