ማሻ፤ የካቲት 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ”ማኒፌስቶ” እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃግብር በሸካ ዞን የማሻ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።
የማሻ ከተማ የመንግስት ተጠሪ አቶ መልካሙ እንዳሻው በመክፈቻ ንግግራቸው ትናንትን በማከም ነገን በመተለም የዜጎችን ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚሠራ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ስድስት መሰረታዊ ችግሮች ቀፍድደው የያዙዋት ሀገር በመሆኗ እነሱም ህብረብሔራዊ አንድነት አለመጣጣም፣ኋላቀርነትና ድህነት ፣ ግጭትና ጦርነት፣የፀና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት አለመኖር፣ ያልተቋጨና ያልተግባባ የሀገረመንግስት ግንባታ፣ ያላትን አጥታ መውጫ ታግታ መኖሩሯ ይሄው የብሔራዊ ጥቅማችንንና ደህነታችንን ይበልጥ አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።
ብልጽግና ይህንን ቀልብሶ ሀገራችን ወደ ተሟላ የጂኦ ፖለቲካ ቁመና ለማምጣት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የማሻ ከተማ ከንቲባ አቶ አንዷለም ጌታቸው የሀገራችን ኢትዮጵያን የእድገት ጉዞ ለማሳካት አሁን ላይ ጂኦ ፖለቲካዊ ብልፅግናዋ እንዲረጋገጥ ብልጽግናን ይምረጡ ሲሉ ጠቁመዋል።
የህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የደ/ም/ኢ/ህ ክልል 11ኛ ክልል ሆኖ የተመለሰው በብልፅግና ፓርቲ በመሆኑ ግጭቶችን ለመፍታትም ዘላቂ መፍትሄ በመስጠት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሰላም ለልማት ልማት ለሰላም በተከናወኑ ተግባራት ላይ በርካቶች ከስራ አጥነት በመላቀቅ የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።
ከግብርና በተጨማሪ በብዘሀ ዘርፍ በኢንድስትሪና በግሉ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ብልፅግና ፓርቲ ተግቶ እየሰራ ይገኛል ነው ያሉት።
በሌላ በኩል የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እንደሀገር የሰንበት ገበያ እየተሰራ በመሆኑ በከተማውም የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር ባመቻቸው ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል።
የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሉዓላዊና በሁሉም የተከበረች ሀገርን ለማስቀጠል ብልጽግናን ይምረጡ ሲሉ ተናግረው የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ሲሆን፣ ምልክቱ የመደመር፣ የአንድነት እና የትብብር ተምሳሌት ነው ብለዋል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች