የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ከተገደሉ በኋላ ኢራን ሦስት አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት ሀገሪቱን በጊዜያዊነት እንዲመራ ማዋቀሯን ይፋ አደረገች። ከፍተኛ ሥልጣን ያለው የሕገ መንግሥት ጠባቂ ምክር ቤት አባል የሆኑት አያቶላህ አሊሬዛ አራፊ ጊዜያዊውን የሽግግር ምክር ቤት እንዲመሩ ተሾመዋል።
ፕሬዝደንት ማሱድ ፔዢሽኪያን እና የኢራን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ ግሖላም ሖሴይን ሞሐሴኒ ኤሼይ የሽግግር ምክር ቤቱ አባላት ናቸው። ጊዜያዊው ምክር ቤት ቋሚ መሪ በባለሙያዎች ምክር ቤት እስኪመረጥ ድረስ ኢራንን የመምራት ኃላፊነት እንደተጣለበት የኢራን ብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ዘግቧል።
ላለፉት 37 ገደማ ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት የ86 ዓመቱ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ትላንት ቅዳሜ መገደላቸውን ኢራን ዛሬ እሁድ ጠዋት በብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ በኩል አረጋግጣለች። የኻሜኒ ሴት ልጅ፣ አማች እና ሴት የልጅ ልጅ ጭምር መገደላቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የእስራኤል ጦር ሠራዊት (IDF) አያቶላህ አሊ ኻሜኒ በተሒራን በሚገኝ የአመራር ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ሳሉ በእስራኤል አየር ኃይል መገደላቸውን አስታውቋል።
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ