ማሻ፤ የካቲት 22/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) አትሌት ታደሰ ታከለ የ2026 የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊ ሆኗል።
አትሌቱ በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒዬም ደረጃ በተሰጠው እና ለ19ኛ ጊዜ የተደረገውን የቶኪዮ ማራቶን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ፈጅቶበታል።
አትሌት ታደሰ ታከለ የባለፈው ዓመት ውድድርም አሸናፊ እንደነበር አይዘነጋም።
በውድድሩ አትሌት ሙክታር እድሪስ 5ኛ፣ሰለሞን ባረጋ ደግሞ 7ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በሴቶች ማራቶን አትሌት ብርቱካን ወልዴ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ሀዊ ፈይሳ ሦስተኛ እንዲሁም አትሌት ሱቱሜ አሰፋ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
ውድድሩን ኬንያዊቷ አትሌት ብሪጅ ኮስጊ በቀዳሚነት አጠናቃለች።
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል