ማሻ፤ የካቲት 13/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የዩናይትድስ ቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ ሐገራት ሸቀጦች ላይ የጣሉትን የቀረጥ ወይም የታሪፍ ጭማሪን የሐገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ዉድቅ አደረገዉ።ወግ አጥባቂ ዳኞች የሚበዙበት የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ፕሬዝደንት ትራምፕ የምጣኔ ሐብት አጀንዳቸዉን ገቢር ለማድረግ የሚጠቀሙበትን የሥልጣን መሳሪያ አግዷል።ትራምፕ ሐገራትን በቀረጥ ጭማሪ ለመቅጣት፣ ለመበቀልና የሚፈልጉቱን እንዲያደርጉ ለማስገደድ የሚጠቀሙት የዓለም አቀፍ አስቸኳይ የኤኮኖሚ ሥልጣን (IEEPA) የተባለዉን ደንብ ነዉ።የዩናይትድ ስቴትስ የመጨረሻ ፍርድ ቤት ዳኞች ዛሬ 6 ለ3 በሆነ ድምፅ ባፀደቁት ዉሳኔ ግን ትራምፕ ተጨማሪ ቀረጥ እንዲጥሉ የIEEPA ደንብ ሥልጣን አይሰጣቸዉም።ፕሬዝደንት ትራምፕ የIEEPA በተባለዉ ደንብ መሠረት በየሐገራቱ ላይ እንዳሻቸዉ የቀረጥ ጭማሪ መጣላቸዉን ከዚሕ ቀደም አንድ የአሜሪካ የበታች ፍርድ ቤት «ሕገ-ወጥ» በማለት ቀረጥ መጨመሩ እንዲቆም ወስኖ ነበር።ይሁንና የትራምፕ አስተዳደር ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤት በማለቱ ዉሳኔዉ አልፀናም ነበር።
#DW Amharic
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ