February 19, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአካባቢ እና ማህበረሰብ  ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት  አማካሪ ድርጅቶች የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመከላከል የሚሰራውን ስራ ማገዝ እዳለባቸው ተገለጸ።

ማሻ፤ የካቲት 12/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቢሮ  በክልሉ ከሚገኑ አከባቢ ናማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ  አማካሪ  ድርጂቶች ጋር  በአከባቢ ጥበቃ መምሪያ አዋጆችና ደንቦች ዙሪያ የምክር መድርክ በቴፒ ከተማ አካሂዷል ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ማሙሸት አምበቻ እንደገለፁት አማካሪ ድርጅቶች የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ረገድ ትልቅ ሚና ስላላቸዉ አሁን ያሉትን ችግሮች በጋራ በመፍታት ዉጤታማ ስራ መስራት እንዳለባቸዉ በመግለፅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አማካሪዎች ለሚፈልጉት ትብብር አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

አክለውም  በESIA ስራ ላይ ሃላፊነት ባለው መልኩ መስራት እንደሚገባ እና  አማካሪ ድርጅቶች በዘርፉ ላይ ለሚፈጠር ችግር ሁሉም እራሱን እዲመለከት እንዲሁም በቀጣይም ሰፊ ስራ እደሚሰሩ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ ለውይይት የሚሆን ሰነድ ያቀረቡት  የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ  አከባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ  ዳይሪክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም ሲሳይ በክልሉ ውስጥ የሚካሂድ ማንኛውም ፕሮጀክት ግንባታ ከመከናወኑና ስራው ከመተግበሩ በፊት የአከባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ተካሂዶ በአካባቢውና በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት የማያደርስ መሆኑ መርጋገጥ አለበት ብለዋል ።

በቂ የሆነ የህዝብ ተሳትፎ ካልተደርገ ተጠያቂነት ማጣት፣ውጤታማ ያለመሆን ና የግጭቶች መከስት ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል ።

የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ምንነት፣ ዓላማና ሊያስገኝ በሚችለዉ ፋይዳ ና  ስለሚታዩ አሉታዊ አስተያየቶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት ዳይሬክተሩ አማካሪዎች እየተጠቀሙ ያለው የሪፖርት ፎርማት ወጥነት ማጣት ፣የወቅታዊነት ፣የተዓማኒነትና የመልዕክት ክፍተት ያለባቸው እንደሆኑም ተጠቁሟል ።

አማካሪዎቹም እደዚህ አይነት መድረክ መዘጋጀቱ እንዳስታቸው ተናግረው በአሰራር ሂደቶች የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና ጠንካራ ሀሳቦችን ይዞ ለመቀጠል በየጊዜው የህግ ተከባሪነት ስራ መስራትና እስከታች ወርዶ የግንዛቤ ስራዎች ላይ ማተኮር  እንደሚገባ አንስተዋል ።

በቀጣሪ በጋራ ለመስራት ማህበር መቋቋም እንዳለበት ሐሳብ ያነሱት አማካሪዎቹ በዘርፉ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰሩም  ተናግረዋል