ማሻ፤ የካቲት 2/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ሰላም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ ጋሻ፣ ጠንካራ የውስጥ አንድነት ደግሞ የማይበገር የሉዓላዊነት ምሶሶ ነው።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበር ውስጣዊ ሰላምን ማጽናት እና ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት ቀዳሚና ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል።
ልዩነቶች እና የፖለቲካ ጥያቄዎች ቢኖሩም እንኳ፣ ከውይይት ይልቅ ጠመንጃን መምረጥ ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ ከማስከፈሉም በላይ ለዕድገቷ ትልቅ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል።
በዚህ ረገድ መንግሥት ለሰላም በሩን ክፍት በማድረግና ተነሳሽነቱን በመውሰድ ረጅም ርቀት መጓዙን ይህም ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
እስከአሁን ጽንፍ ይዘው የቆሙ አካላትም በተመሳሳይ ልዩነቶችን ከሀገር በታች በማድረግ እና በሀሳብ የበላይነት በመሞገት ለውስጣዊ ሰላም መጽናት የዜግነት ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ይገልፃሉ።
ፍትሐዊ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥም ሰላምን በማጽናት ሂደት መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ መንግሥት በሙሉ አቅሙ እየሠራ ይገኛል።
በጥቅሉ የኢትዮጵያውያን ውስጣዊ አንድነት መጠናከር የመደራደር አቅማችንን ከፍ በማድረግ ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር እንደ ብርቱ ክንድ ሆኖ ያገለግላል።
በመሆኑም ሀገራችን አሁን ላይ እየተከተለችው ያለው ገቢር ነበብ (Pragmatic) ዲፕሎማሲ ይበልጥ ስኬታማ እንዲሆን፣ ውስጣዊ ሰላምን ማጽናት ወቅቱ የሚጠይቀው እውነተኛ አርበኝነት ነው።
ሁላችንም ለሀገራችን ሰላም እና ለጋራ ብልጽግናችን በቁርጠኝነት እንነሳ።
More Stories
ለ7ኛዉ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ ይምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ተካሂደዋል ።
ጋዜጠኞች ሙያቸውን እና ሕግን እንዴት መከተል እንዳለባቸው ሊያውቁ ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።