ማሻ፤ ጥር 21/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) መምህር ዳኪቶ ጋወቶ አብሮዋቸዉ ከሚሰሩ የቋንቋ ጥናት ቡድን ጋር በመሆን ከነሃሴ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሬዲዮ ጣቢያችን “የሺቲ” በሚል ስያሜ ሳምንታዊ ፕሮግራም የሸክኖኖ ቋንቋን በሬዲዮ በማስተማር ለቋንቋዉ ዕድገት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለዉለታ ነበሩ፡፡
መምህር ዳኪቶ ጋወቶ በመምህርነት ሙያ ረጅም ዓመታት ያገለገሉና ትውልድ በመልካም ስነምግባር ታንጾ እንዲያድግ የራሳቸውን ድርሻ የተወጡ መምህር ነበሩ ።
ከ1988 ዓ,ም ጀምሮ የሸክኖኖ ቋንቋ ጥናት ቴክኒክ ኮሚቴ አባል ሆነዉ በመስራት ላይ የነበሩና ከ2000 ዓ,ም ጀምሮ ደግሞ የሸኪኖኖ መጽሃፍ አዘጋጅና ኤድተር በመሆን ሲያገለግሉ እንደቆዩም ከህይወት ታሪካቸዉ ለማወቅ ተችሏል።
እኝህ አባት ባለትዳር እና የ3 ወንድ እና የ4 ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ ሰኔ 28/1954 ዓ,ም ተወልደዉ በተወለዱ 63 ዓመታቸዉ በድንገተኛ ሞት ከዚህ ዓለም ተለይተዋል፡፡
ሥርዓተ ቀብራቸዉም ጥር 21/ 2018 ዓ.ም በማሻ ሐመረኖህ ቅድስት ድንግል ማርያም በተክርስትያን ተፈፅሟል።
የደቡብ ሬድዮና ቴለቪዥን ድርጅት የማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ ለመምህር ዳኪቶ ጋወቶ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸዉ ፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉና የስራ ባልደረቦቻቸዉ መፅናናትን ይመኛል።
More Stories
በመስክ ምልከታው የተገኘው ልምድ የሌማት ትሩፋት አካል በመሆኑ አርሶ አደሮቻችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባል፦
የኢራን አዲሱ መንፈሳዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ …
የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ባለቤትነት ጥያቄ ለቀጣናዊ ሰላም ያለው ፋይዳ