ማሻ፤ ጥር 20/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በመድረኩ በዞኑ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም በማስፈን ሁለንተናዊ የዞኑን ልማታዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ለማሳደግ የጋራ ተግባቦት መፍጠር እና በመግባባት መስራት ላይ ስምምነት መደረሱ ተገልጿል።
ወቅታዊ የዞኑን የፀጥታ ሁኔታዎችን የሚዳስስ ሰነድ እና የፀጥታ ግብረ ሃይል ዕቅድ በዞኑ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን አውሎ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ማንኛውም የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት አስተማማኝ ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለሰላም ቅድሚያ መስጠት አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
የጸጥታ ስራ ውጤታማ እንዲሆን በየቀኑ የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባና በዚህም ሂደት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በጸጥታ ኃይሉ በአመራሩና በህብረተሰቡ የተቀናጀ ጥረት በዞኑ ሰላም መስፈኑን ገልጸው፤ ይህን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል መላው አመራር በቁርጠኝነት መረባረብ እንዳለበት ገልጸዋል።
ሰላምን ለማረጋገጥ ከወትሮው በተለየ መንገድና በላቀ ዝግጁነት መስራት እንደሚገባ የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው፤ በአጎራባች ዞኖች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች በዞኑ ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድሩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ህገወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርን በተጠናከረ መንገድ ለመከላከል፣ የፀጥታ ግብረሀይሉና የህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ግብረሀይል በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የሸካ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን አውሎ በበኩላቸው በአጎራባች ክልሎችና ዞኖች የሚታዩ ግጭቶችን በውይይት እና በመግባባት በመፍታት ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ህገወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል በቅንጅት የተጠናከረ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአጎራባች አካባቢዎች የሚታዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራና ማንኛውንም የጸጥታ ስጋት ቀድሞ የመከላከል ስራ እንደሚከናወን የገለፁት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተወካይ ኮሎኔል አስራት ወ/ሚካኤል ናቸው።
በዞኑ የሚታዩ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን በጥብቅ ክትትልና በውይይት በመፍታት ረገድ የፀጥታ ኃይሉ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀው በዚህም የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ታከለ ታደሰ በበኩላቸው በየደረጃው የሚገኘው የፀጥታ መዋቅር ለቀጣይ ተልዕኮ ራሱን በብቃት ማዘጋጀት እንዳለበት ገልጸው የፀጥታ ስራዎችን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሚስተዋሉ ህገወጥ ንግድና የፀጥታ ስጋቶችን በቀጣይነት በመከታተል፣ በውይይትና በመግባባት መፍታት እንደሚገባም አስገንዝበዋል ኮሚሽነሩ።
ህገወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርን በቅንጅት እና በተጠናከረ መንገድ መከላከል እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ አመላክተዋል።
በህዝቦች መካከል መጠራጠር ለመፍጠር እና ሰላምንና ልማትን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎችን በህግ አግባብ መቆጣጠር እንደሚገባ የመድረኩ ተሳታፊዎች አጽንኦት ሰጥተዋል። ዘገባው የዞኑ መ/ኮ ነው
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያና አሜሪካ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በጋራ ለመስራት ተስማሙ