ማሻ፤ ጥር 15/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሀገራዊ ኢንሼቲቭ በሆነው በፋይዳ መታወቂያና 5 ሚሊየን ኢትዮ-ኮደርስ መድረክ ተካሂዷል ፡፡
በመድረኩ የተገኙት የቢሮው ምክትል ኃላፊና ኢኖቬሽንና ተክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስፋው እንዳሉት÷ዜጎችን በእዉቀት፤በክህሎትና በአመለካከት በማብቃት የስራ ዕድል በመፍጠር ሀብት ለማካበት የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ- ኮደርስ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግስት የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይ ለማሳካት ባለፉት አምስት አመታት አበራታች ስራዎች መስራቱን የገለጹት አቶ ምትኩ በ2030 በክህሎት የበቃ የሰዉ ሀይል ለማፍራት የዲጂታል ስትራቴጂ ክህሎት ፕሮግራሞችን በመንደፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ሀገሪቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ኋላ ቀር በመሆኗ ፤ዜጎችን በእዉቀት፤በክህሎትና በአመለካከት በማብቃት ሀብት ለመፍጠር እንዲሁም መንግስታዊ አገልግሎቶች ዲጂታል ለማድረግ ታስቦ ሀገራዊ ኢንሼቲቭ የሆነዉ “5 ሚሊዮን ኮደርስ” ፕሮግራም ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በክልሉን ዜጎች ‘5ሚልዮን ኢትዮ-ኮደርስ” ፕሮግራም ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ምትኩ በእስከ አሁኑ ወደ 28ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ኮደርስ ስልጠና እየተከተሉ መሆናቸዉን ተናግረዉ ከእነዚህ ዉስጥ 7ሺህ 953ቱ ሴርተፊኬት መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
እንደ ክልል በአመቱ መድረስ ከሚገባዉ ዕቅድ አንጻር ዘርፉ የተጠናከረ ስራ እንደሚፈልግም ጠቁመዋል ።
የዲጂታል ፋይዳ አገለግሎት በሚመለከትም በክልሉ ባለፉት 6 ወራት 246ሺህ 436 ዘጎች ተጠቃሚ መሆናቸዉን ገልጸዉ ይህም በክልሉ ተደራሽ ለማድረግ ከታቀደዉ 1ሚልዮን 900 በላይ ዘጎች ቁጥር አንፃር ቁጥር ትንሽ በመሆኑ በተቀሩት ወራት በተቀናጀ አኳሃን የአገለግሎቱ ተጠቃሚ ዘጎችን ቁጥር ለመጨመር እና ዕቅዱን ለማሳካት በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
መተማመን በመፍጠር ዋስትና በመሆን እያገለገለ የሚገኘዉ የዲጂታል መታወቂያ ሁሉም ዘጎች ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ምትኩ “ተክኖሎጂ መጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን ግደታ “መሆኑን በማወቅ ሁሉም ዘጎች የፋይዳ መታወቂያ በማዉጣት ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል ።
የካፋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታደሰ በዞኑ ለ17 ሺህ 200 ለሚሆኑ 5 ሚሊየን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ባለፉት 6 ወራት ለ5ሺህ 200 ሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ሰርትፋይ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
ከፋይዳ ድጂታል መታወቂያ አኳያም በበጀት ዓመቱ ለ711ሺህ 917 ዜጎች የድጂታል መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን አፈጻጸሙ 140 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የድጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል ይህም ከታቀደው ዕቅድ አንፃር ዝቅተኛ በመሆኑ በቀጣይ ወራት ዕቅዱን ለማሳካት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል፡
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።