ማሻ፤ ጥር 15/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 46ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡
በዚህም መሠረት፦
1ኛ.የቀረቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቷል። በዚህም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን በግብርና 27፣ በኢንዱስትሪ 4 እና በአገልግሎት 2 በአጠቃላይ 1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎችን መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።
2ኛ. መስተዳድሩ ምክር ቤቱ የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ወደ ምክር ቤት መርቷል። እንዲሁም የታክስ አስተዳደር ደንብ መርምሮ አጽድቋል።
3ኛ. መስተዳድር ምክር ቤቱ የገጠር ኮሪደር ሥራዎች ዙሪያ ተወያይቶ አቅጣጫ ማስቀመጡን ከክልሉ መ/ኮ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ