ማሻ፣ ታህሳስ 17/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና በአፍሪካና በዓለም መድረክ የሚኖራትን ተፅዕኖ ከፍ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው አሉ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፡፡
48ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ “ብሔራዊ ጥቅምና መገናኛ ብዙሃን” በሚል መሪ ሃሳብ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና በአፍሪካና በዓለም መድረክ የሚኖራትን ተፅዕኖ ከፍ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በመገንባትና ለሰላምና መረጋጋት ቅድሚያ በመስጠት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
መገናኛ ብዙሃን ሀገርን በመንባት ሂደት ውስጥ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልጸው፥ በቀጣናው እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያ ተፅእኖ ፈጣሪነትና የልማት ስራዎችን በማስጠበቅ መስራት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።
በፍጥነት እያደገ በሚገኘው ዲጂታል የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በማጥራት ለሀገረ መንግስት ግንባታ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመድረኩ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡
#ኤፍ ኤም ሲ
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።