ማሻ ፣ የሰኔ 30፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በሸካ ዞን የኪ ወረዳ አላሞ ቀበሌ ከ37 ሚለዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ ተመርቆ ክፍት ሆኗል ።
ፕሮጀክቱ ከ66 ሄክታር በላይ ማሳ ማልማት እንደሚችልና 1መቶ 60 በላይ አባዎራዎችን ተጠቃሚ እንደምያደረግ ነው የተገለጸው ።
በተጨማሪ በዞኑ ቴፒ ከተማ ላይ በመንግስት እንዲሁም በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባው የጎጅ ድልድይን ጨምሮ ሌሎችም ፕሮጀክቶች እንደምመረቁ ነው የተጠቆመው ።
በዚህ የምረቃ ፕሮግራም ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾን ጨምሮ የክልል፣ የዞን ፣የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል ።
አስቻለው አየለ
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።