ማሻ ፣ የግንቦት 12፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ወረዳው ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል ።
በበልግ አዝመራዉ በእንሰት፣በቦቆሎ፣በድንች፣በአተክልትና ፍራፍሬ እንድሁም በቦሎቄ ከ8 ሺህ 656 ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 6ሺህ 932 ሄክታር መሸፈን መቻሉን የአንድራቻ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አክልሉ ሸነኖ አስታዉቋል።
ወረዳዉ ለእንሰት ተክል በሰጠዉ ትኩረት በ3 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ 12 ሚሊየን የእንሰት ችግኝ ለመትከል አቅዶ በ2 ሺህ 687 ሄክታር መሬት ላይ በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ 9ነጥብ 5 ሚሊየን የእንሰት ችግኝ መተከሉንም ገልፀዋል።
ከዕቅዱ ቀሪ 2.5 ሚሊየን የእንሰት ችግኝ በመጪዉ ዓመት በሚተከለዉ ተጨማሪ ሆነዉ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በበልግ አዝመራ የተተከሉትና የተዘሩ ሰብሎች ውጤታማ ለማድረግ አርሶ አደሩ የአረም ሳምንታትን ተከታትሎ በመቆጣጠርና በመንከባከብ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባም ጠቁመዋል ።
ዘጋቢ ግርማ ጮሪቶ
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።