ማሻ ፣ የግንቦት 12፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) “በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ዲጂታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ ምሦሶ ተሻሽሏል።
ከአሁን በኋላ አማራጭ ሳይሆን ሰዎችን ከአገልግሎቶች፣ ከማኅበረሰቦች፣ ከተቋማት እና ከመንግሥታት ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መሠረተ ልማት ነው።
ከአምስት ዓመት በፊት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ራዕይ እየተመራን እጅግ አስፈላጊ ውሳኔ ወስነናል።
ይህም ዘመናዊ፣ አካታች፣ መሠረት ያለው እና ሊሰፋ የሚችል ዲጂታል የማንነት ሥርዓት መገንባት ነው። ይሄንንም ለእያንዳንዱ ነዋሪ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ነበር።
ይሄንን ሥርዓት ‘ፋይዳ’ ብለን እንጠራዋለን። ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም። የግለሰቦችን ግላዊ መረጃዎች ምሥጢራዊነት በመጠበቅ እና አስፈላጊ የሆነውን ብቻ በማጋራት ማንነትዎን የሚያረጋግጥ ልዩ መለያ ቁጥር ነው!”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።