ማሻ ፣ የግንቦት 09፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ለአፍሪካ” መርሃ ግብር ላይ፥ አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አንሰተዋል።
ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች መሆኑን አውስተዋል።
እንደ ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቲዮት፣ ዲጂታል መታወቂያ ብሎም “የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ” ባሉ ፕሮግራሞቿ ኢትዮጵያ ሕልሞቿን ወደ ተጨባጭ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተግባራት መለወጥ ችላለች።
በ2030 ማንም ወደ ኋላ በማይቀርበት አኳኋን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን በራሷ መልክ በሥነምግባር፣ በአካታችነት እና ዘላቂነት ቅርፅ ማስያዝ እንደሚኖርባት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስምረውበታል።
More Stories
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከኅብረተሰቡ መረጃ የሚቀበልበትን የኮምዩኒኬሽን ፕላትፎርም ይፋ አደረገ
⛔️አስቸኳይ የሳይበር ደህንነት የጥንቃቄ መልዕክት
ጨረቃ ላይ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የመገንባት ህልም