ሙሉ በሙሉ በፀሐይ ኃይል የሚሠራ አዲስ አነስተኛ ትራክተር በማላዊ ወደ አገልግሎት ገብቷል።
“አፍትራክ” (Aftrak) የተሰኘው አነስተኛ ትራክተር፤ በታዳሽ ኃይል የሚሠራ የግብርና ሜካናይዜሽን መሣሪያ መሆኑ ተመራጭ አድርጎታል።
በማላዊ ምርትን የሚያሳድጉ የግብርና አሠራሮችን ሲተገብር የቆየው ‘ቲዬኒ’ የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት እንዳስታወቀው፤ ቴክኖሎጂው የሰብል ምርትን ከሁለት እጥፍ በላይ ከመጨመር ባሻገር፣ የማላዊ አርሶ አደሮችን ገቢ እስከ ዘጠኝ እጥፍ ሊያሳድግ ይችሏል።
በፀሐይ ኃይል የሚሠራውን አዲስ አነስተኛ ትራክተር ሙሉ በሙሉ ለማንቀሳቀስ በቀን 7.5 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ቴክኖሎጂውን ተደራሽ ለማድረግ በማላዊ ለሚገኙ የአርሶ አደር ማኅበራት በቅናሽ ዋጋ ለማቅረብ መታቀዱ ተመላክቷል።
በተጨማሪም ለመግዛት አቅሙ የሌላቸው አርሶ አደሮች ትራክተሩን በሰዓት ተከራይተው እንዲጠቀሙ የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ የማበልጸግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።
በማላዊ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ፣ በቀጣይም ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደሚስፋፋ ይጠበቃል።
More Stories
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱ ክንፍ፤ የቢሾፍቱ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ
በቻይና የተሰራው የዓለማችን ግዙፉ የጭነት ድሮን
የነዳጅ ዘመን እያበቃ ይሆን? በ2030 የታዳሽ ኃይል አጠቃቀም በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምር ነው