መጋቢት 26፣ 2017 ቤልጂየማዊው የማንቼስተር ሲቲ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዲብሮይን ከዘጠኝ ዓመት ቆይታ በኋላ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከቡድኑ ጋር እንደሚለያይ ተረጋግጧል፡፡
ተጫዋቹ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት በውድድር ዘመኑ መጨረሻ የሚጠናቀቅ በመሆኑ በነፃ ዝውውር ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በክለቡ ቆይታው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን ማሳካት የቻለው ኬቨን ዲብሮይን፤ በማንቼስተር ሲቲ ቤት በ412 ጨዋታ ተሰልፎ 106 ጎሎችን አስቆጥሯል።
174 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ኬቨን ዲብሮይን ከማንቼስተር ሲቲ ጋር በውድድር ዓመቱ መጨረሻ እንደሚለያይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ የገለፀ ሲሆን ደጋፊዎቹን አመስግኗል፡፡
የሳውዲ ክለቦች የተጨዋቹ ፈላጊ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን የተጫዋቹ ቀጣይ መዳረሻ የሳዑዲ አረቢያ ሊግ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
More Stories
ኢትዮጵያዊ በዳምጠው ከበደ ተጨማሪ ሜዳሊያ አገኘች
ቴፒ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
የኤሲሚላን የቀድሞ ተጫዋች ፍራንኮ ባሬዚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ