ማሻ ፣ የመጋቢት 08፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 57ኛው አህጉራዊ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባዔው ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፣ የአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ፣ ሚኒስትሮች፣ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጉባዔው“የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን የሚያፋጥኑ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን መቀየስ”በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ የአፈጻጸም ሒደትና የቀጣይ ተግባራት ላይ በመምከር አቅጣጫ ማስቀመጥ የጉባዔው ዋነኛ አጀንዳ ነው ተብሏል፡፡
ፋና
More Stories
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ባቀረቡ ቅሬታ መሰረት በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ ተወሰነ።
ጳጉሜ 3 “የፅናት ቀን” በቦንጋ ከተማ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት