በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል ባለው አጠቃላይ የፖለቲካ፣ የአስተዳደር እና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ካሉ የፖለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።በውይይቱ ወቅት፥ በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል።ይህን ተከትሎም በተለዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በትብብር በመስራት የክልሉን ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ ተደርሷል።በተለይም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀዬአቸው እና የቀድሞ ታጣቂዎችን ደግሞ ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለስ ሥራ በሚሳለጥበት እና በበለጠ ትኩረት በሚሰራበት ሁኔታ ላይ መግባባት ተፈጥሯል።በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀም የህዝብን እና የሀገርን ጥቅም በሚያስጠብቅ ሕጋዊ አግባብ እንዲከናወን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግሥት አገልግሎቶችም የህዝብን ፍላጎት በሚመጥን አግባብ እንዲሻሻሉ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ በውይይቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።በመጨረሻም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ክልላዊ ምርጫ እስኪያካሂድ ድረስ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቅቋል።
EBC
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።