በመቐለ፣ አዲግራት፣ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል። በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ተገኝተው ፈተናውን ያስጀመሩት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ተማሪዎች በፈተናው የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲሰሩ መልእክት አስተላልፈዋል። ተፈታኝ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲገቡ መልካም ምኞታቸውንም ገልፀዋል። በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች 23ሺህ ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን አስታውቀዋል። ተፈታኞች በ2013/14 ትምህርት ዘመን በቀድሞ ስርአተ ትምህርት ተምረው በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ሳይወስዱ የቆዩ መሆናቸው መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።
EBC
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች