በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ 2ኛ መርሐ ግብር ዛሬ ተጀምሯል። በምድብ 1 አዘጋጇ አገር ጀርመን ከሀንጋሪ ጋር ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በስቱትጋርት አሬና ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ በጀርመን 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።ለጀርመን የማሸነፊያ ግቦቹን ሙሲያላ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እና ጉንዶጋን ከረፍት መልስ ከመረብ አሳርፈዋል።ጀርመን በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ ስኮትላንድን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፏ ይታወሳል።እናም የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ጀርመን ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቷን ያረጋገጠች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች።ጀርመን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን እሁድ ከስዊዘርላንድ ጋር የምታደርግ ሲሆን፤ ሀንጋሪ በበኩሏ ከስኮትላንድ ጋር ትጫወታለች።
EBC
More Stories
የ2026 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ …
ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነቷ እንዲሰረዝ መወሰኑ አሳፋሪ ነው፡- የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኦጉስቲን ሴንግሆር
ቦርንማውዝ ከ ማንችስተር ዩናይትድ