ማሻ፣ ታህሳስ 27/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የዞኑ የቆዳ ስፋት በአብዛኛው በደን የተሸፈነ በመሆኑ በውስጡ በርካታ ታርካዊና ተፈጥሯዊ መስቦችን ይዞ ይገኛል።
በዞኑ ዉስጥ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ታርካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መዳረሻዎችን በጥናት የመለየት ስራ መከናወኑን በባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የቱሪዝም ፕሮሞሽንና ግብይት ቡድን መሪ አቶ ብርሃኑ አያሾ ተናግረዋል፡፡
በማሻ ወረዳ ዉስጥ የሚገኙ የሸክሸኮ እና ጋሀማዎ ዋሻና ፏፏቴ፤ በአንድራቻ ወረዳ ጋንዲዎቺ የተራራ ላይ ሀይቅና ሌሎች የቱሪስት መዳረሻዎችን ለጎብኝዎች ምቹ በማድረግ ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን አቶ ብርሃኑ ጠቅሰዋል፡፡
በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ዋሻዎች ከቱሪስት መስብነት ባሻገር በተለያዩ የጦርነት ጊዜያት የአካባቢዉ ማህበረሰብ ንብረቱንና ራሱን ለመከላከል ዋሻዎችን እንደመጠልያ ይጠቀምበት እንደነበር ተገልጧል።
በዞኑ የማሻ ወረዳ ነዋሪዎች ወጣት ሰዉዓለም በቀለ እና አቶ አስታዉሰኝ እንደሻዉ የመስህብ ስፍራዎች በአባቶቻችን ብርቱ ጥረት ተጠብቀዉ የቆዩ በመሆናቸዉ አሁን የመንከባከብና የመጠበቅ ሓላፍነት በእኛ ላይ በመሆኑ አየተወጣን ነዉ ብለዋል፡፡
በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች ምቹና ማራኪ በመሆናቸዉ በሀገር ውስጥና ውጭ የሚገኙ ጎብኝዎች አካባቢውን እንዲጎበኙ አቶ ብርሃኑ አያሾ ጥሪ አቅርበዋል
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች