ማዕከሉ ለአከባቢው ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባሻገር ለበርካቶች የስራ ዕድልን መፍጠሩ ተገልጿል።
የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች እንደገለፁት የቡና ቅምሻ መዕከሉ ወደ ስራ መግባቱ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለአከባቢው እድገት ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።
የቡና ቅምሻ ማዕከሉ በአካባቢው አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ከዚህ ቀደም በሂደቱ የነበሩ የተለያዩ እንግልቶች መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሴርትፍኬሽን ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል ሻወኖ ተቋሙ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የታጠበ ቡና 3ሺ 5መቶ 63 ቶን ያልታጠበ 18ሺ 27ቶን ባጠቃላይ እስካሁኑ ከ21ሺ 5መቶ 90 ቶን በላይ የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉን ገልፀዋል።
ማዕከሉ ከዚህ በተጨማሪ ለአከባቢው ማህበረሰብና ለከተማው ከፍተኛ ገቢን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ጠቁመው የቡና ጥራትን ለማስጠበቅ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑንና ተቋሙ ለአጎራባች ክልሎችም ጭምር አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች
የአራዳ ፓርክ የነዋሪዎችን ሰብአዊ ክብር ያስቀደመ ፕሮጀክት ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ