የጤና ዘርፍ የአገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም አተገባበር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚረጋገጠው ጤናማ ትውልድ ማፍራት ስቻል ብቻ መሆኑ ታምኖበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የጤና ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም ተካሂዶ በየደረጃው ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
ሪፎርሙ ከቢሮ ተቋማት እስከ ሰው ድረስ ሁሉ አቀፍ ለውጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀው ለሰራተኛውና ለተገልጋዩ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል።
ተገልጋይ ክህሎት የታከለና ብቃት ያለ አገልግሎት ይጠብቃል ያሉት ሀላፊው ሪፎርሙ ብዝሃነትንና ብቃትን አጣምሮ በማስኬድ ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳም ጠቁመዋል።
የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፤ ቅልጥፍናና ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ በሪፎርሙ ትኩረት ከተሰጠባቸው ነጥቦች አንዱ የጤና ዳጂታላይዜሽን እንደሆነም አቶ ኢብራሂም ተማም ገልፀዋል። ይህ የጤና ዲጂታላይዜሽን በተለይ ወረቀት አልባ አገልግሎትን በማስፋፋት ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለማቅረብ ይረዳል ብለዋል።
የሰራተኞች ሚዘና ስርዓቱ ከህዝብ ተጠቃሚነትና ከተቋማት ውጤታማነት ላይ የተመሰረተ በማድረግ የህዝብ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ የቀረበ ሪፎርም እንደሆነ ገልጿል።
ሪፎርሙ የጤናውን ዘርፍ አገልግሎት ለማሻሻልና ለማዘመን ሁኔኛ መፍትሔ በመሆኑ በሙሉ አቅም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አቶ ኢብራሂም ተማም ጠይቀዋል።
ለወረርሽኝና ለድንገተኛ አደጋ የማይበገር የጤና ስርዓት ለመዘርጋት የጤና ዘርፍ አገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርምን በሙሉ አቅም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ።
More Stories
የሙዝ የጤና ጥቅሞች 🤍
5ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በአል ፋሊህ አካዳሚ ተጀመረ ።
ከ90 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ አውደርዕይ ሊካሄድ ነው