ማሻ፣ ታህሳስ 27/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሊከሰት የሚችል ማንኛውም ችግርና ድንገተኛ አደጋ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ክስተቶችን መከላከል በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በቂ ዝግጅት መደረጉን መምሪያው ገልጿል ።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የገና በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት መደረጉን የሸካ ዞን ፓሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስታውሰኝ አይሞ ተናግረዋል ።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሊከሰቱ የሚችሉ ዝርፊያ ፣ ንጥቂያና ሌሎች የማጭበርበር ወንጀሎችን ቀድሞ መከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት መደረጉን ምክትል ኮማንደሩ ገልፀዋል ።
በበዓል ሰሞን የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት የትራፊክ ፖሊስ ከሚያደርገው ቁጥጥርና ክትትል በተጨማሪ አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ አሳስበዋል።
ከበዓል ስራዎች ጋር ተያይዞም የእሳት አደጋ ሊፈጠር የሚችል በመሆኑ በተለይ በቤት ውስጥ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ጭምር ተናግረዋል ።
በበዓል ወቅት ለጸጥታ ስጋት የሆኑ እንቅስቃሴዎች ሲያጋጥሙ ህብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት የድርሻቸውን እንዲወጣ ያሳሰቡት ምክትል ኮማንደር አስታውሰኝ በዓሉ የሰላም ፣የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል ።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች