በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሷል፡፡ በኤምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡
በመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በስፔን አንድ አቻ ተለያይቶ የተመለሰው አርሰናል በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
በዚህ ዓመት በሻምፒዮንስ ሊግ አንድም ጨዋታ ያልተሸነፈው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በአውሮፓ ትልቁ የክለቦች ውድድር ከ20 ዓመት በኋላ የደረሰበትም ምሽት ሆኗል፡፡
አርሰናል በቡዳፔስት በሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ከባየር ሙኒክ እና ፒኤስጂ አሸናፊ የሚገናኝም ይሆናል፡፡
More Stories
ማንቼስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋገጠ
ኬንያዊው አትሌት በሽልማት ተንበሸበሸ
የቀድሞ ብቃቱ ላይ የማይገኘው ቡካዮ ሳካ