ማሻ፣ ታህሳስ 27/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የአንድራቻ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ነዋሪዎቹ ያነሱት ቅሬታ ተገቢ መሆኑን በመግለጽ ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።
በጌጫ ከተማ በተለያዩ መንደሮች ተገኝተን ካነጋገርናቸው ነዋሪች መካከል ወ/ሮ ውድነሽ ከበደ፣ አቶ አጥናፉ አመያ እና መ/ር አመነ አሰፋ እንደተናገሩት በ2017 ዓ/ም በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተከፈቱና ጥገና የተደረገባቸው የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተስፋ ሰጪ እንደነበሩ አንስተዋል ።
ይሁን እንጂ በመንደራቸው የተከማቸ ጠጠር ባለመበተኑ ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ እንደሆነ ተናግረዋል ።
ጣቢያችን ጉዳዩን አስመልክቶ ከወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሳምነው አይኔ ጋር ባደረገው ቆይታ አስተዳዳሪው እንዳነሱት ቅሬታው ተገቢ መሆኑንና በቅርቡ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የከተማ መሠረተ ልማትን ለማሳለጥ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ በቅርቡ ወደ ስራ የሚገባ እንደሆነ አስረድተዋል ።
አስተዳዳሪው በየዓመቱ በተለያዩ የልማት ተግባራት ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረው በተያዘው በጀት ዓመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
በ2017 ዓ/ም በሸካ ዞን ጌጫ ከተማ ለውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ የተከማቹ ጠጠሮች ባለመበተናቸው ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች