ማሻ ፣ የግንቦት 10፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት ፑቲን በስልክ ለመመከር ቀጠሮ መያዛቸውን ከክሬምሊን የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል::
የኢስታንቡል የሰላም ውይይትን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ለመምከር ቀጥሮ መያዛቸውን በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል::
የሁለቱ መሪዎች የስልክ ውይይት ለነገ ሰኞ ቀጠሮ የተያዘለት ስለመሆኑ ክሬምሊን አረጋግጧል::
የመሪዎቹ ውይይት የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እንዲያበቃ በሚያስችል ጉዳይ ላይ እንደሚሆን ይጠበቃል::
የሁለቱ ሀገራት የንግድ ጉዳይ በፕሬዝዳንቶቹ የስልክ ውይይት ላይ የሚነሳ ሌላው አጀንዳ እንደሚሆንም ይጠበቃል::
ፕሬዝዳንት ትራምፕ “የሩስያ ዩክሬንን ሰላም ማምጣት የምችለው እኔ ነኝ” ማለታቸው የሚታወስ ነው ሲል ቲአርቲ ዘግቧል::
More Stories
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች
ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የጠፈር ጣቢያዋን ለውጭ ሀገር ጠፈርተኞች ክፍት አደረገች