ማሻ ፣ የግንቦት 11፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በካንሰር ህመም መጠቃታቸውን ጽ/ቤታቸው አስታውቋል።
የ82 አመቱ ጆ ባይደን በከባድ የፕሮስቴት ካንሰር መጠቃታቸውና በካንሰር የተጠቃው ህዋሳቸው ወደ አጥንታቸው መዛመቱ ተነግሯል።
የፕሬዚዳንቱ የካንሰር ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ በሚደረግላቸው የህክምና አማራጮች ዙሪያ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እየመከሩ ነው ሲል አሶሺየትድ ፕረስ ዘግቧል።
የወቅቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጆ ባይደን ባስተላለፉት መልዕክት፥ በሁኔታው ማዘናቸውን ገልጸው ከህመማቸው በፍጥነት እንዲያገግሙ ተመኝተዋል።
ፋና
More Stories
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች
ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የጠፈር ጣቢያዋን ለውጭ ሀገር ጠፈርተኞች ክፍት አደረገች